1.
እራስህን ንቀን ቃልህን አቃለን
መንፈስህ ሲወሰን ሁሌ እንሰማለን
ሥጋ ብቻ ሆነን በአመፅ ተውጠናል
እራስን መመርመር ፍፅም አቅቶናል
በከፍታ ስፍራ በሰማይ ያለኸው
ምንም አይሳንህ ሁሉን ቻይ የሆንከው
ልብ ኩላሊትን የምትመረምረው
ጌታ ሆይ ጓዳችንን አፅዳ አጥበህ አስተካክለው
2.
ያኔ ስትልከን ጦር እቃህን ሰጥተህ
ኃይል በኃይል አድርገህ ሞገስ አከናንበህ
ከጦር ሜዳው ወጥተን ድልን ሰጥተኸናል
ዛሬ ግን ወዮልን ጠላት ዝቶብናል
3.
እንደ ቀድሞ መስሎን እንዋጋ ብንል
በብዙ ለማጥመድ መረቡን ብንጥል
ከንቱ ልፋት እንጂ ምርኮ ከየት ይምጣ
ግራ ተጋብተናል በከንቱ እሩጫ
4.
አሁን ተረድተናል ኃጢአት አድርገናል
በትዕቢት ፍላጻ አስለቅሰናል
በእርማችን ምክንያት ፊትህ ከብዶብናል
ጌት ሆይ ታረቀን ማረን ብለንሃል